አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ኅዳር ስድስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብርት እናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከስደት በሚመለሱ ጊዜ ወደ ደብረ ቁስቋም ገባ በመንገድም ጉዞ ካገኛችው ድካም አረፉ፡፡

ዳግምኛም በኋላ ዘመን በዚህ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቶቹን  ሰብስቧቸው ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጣቸው፡፡

ለዚህም የእስክንድርያ ሀገር ሊቃነ ጳጳሳት፣ ቅዱሳን አባቶቻችን ቄርሎስና ቄዎፍሎስ ምስክሮች ሆኑ፡፡

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

አምላክን የወለደች የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ ከእኛ ጋር ይኑር።

ለዘላለሙ አሜን!

ምንጭ፤ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር