የጄኔቫ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (06 November 2022) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የጀርመን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በተገኙበት ይከበራል።

በበዓሉ ላይ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ካህናት፣ ምዕመናን፣ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እንዲሁም በጄኔቫ ውስጥ የሚገኙ የሌሎች አገሮች አብያተ ክርስቲያን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ፡፡

ቅዳሜ ማታ ለእሁድ አጥቢያ ከሌሊቱ 6 ሰዓት (00:00H) ጀምሮ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ማኅሌተ ቅዱስ ያሬድ ኢትዮጵያዊ ይካሄዳል ::