Events Calendar

Wednesday 23 November 2022
የነብያት ጾም መግቢያ
Wednesday 23 November 2022
Hits : 63

ነገ ማግሰኞ ኅዳር ፲፫ ቀን ፳፻፲ወ፭ (22/11/2022) ዓ ም የነቢያት ጾም ቅበላ ነው፤ ይኽ ጾም የገና ጽም በመባልም ይታወቃል።

ነቢያት ጌታ ይወርዳል ይወለዳል እያሉ በትንቢት መነጽርነት የጌታን ሰው መሆን ተረድተው በተስፋ የጾሙት ጾም ነው።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ይኽን ታላቅ ወቅት በሐዲስ ኪዳን ከተጾሙት አምስት አጽዋማት ማለትም

፩ -  ዐቢይ ጾም ወይም ጾመ ሁዳዴ እንዲሁም ጾመ ኢየሱስ፥ ተብሎ የሚጠራው የጌታ ጾም ማቴ ፬፥፩

፪ -  ጾመ ረቡዕ ወዓርብ (ጾመ ድኅነት) የጌታችን ምክረ ሞቱ የተፈጸመበትና ጌታ የተሰቀለበት።

፫ -  ጾመ ሐዋርያት "በተለምዶ የሰኔ ጾም" የሚባለው።

፬ - ጾመ ፍልሰታ ከነሐሴ 1-15 ቀን ድረስ የሚጾመው የመቤታችን ጾም የዚህም ጀማሪዎች ሐዋርያት ናቸው።

፭ - ጾመ ገሃድ የመገለጥ ጾም ይኽም ጾም ተውላጠ ረቡዕ ወዓርብ ይባላል ምክንያቱም ልደትና ጥምቀት ረቡዕና ዓርብ ላይ በሚውሉበት ጊዜ ለበዓላቱ ክብር ሲባል በመንፈቀ ሌሊት ቅዳሴ ተቀድሶ ጾሙ በሌሊት ስለሚፈታ በዋዜማው ያለው አንድ ቀን ይጾማል። ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት አምስቱ መነሻቸው ሐዲስ ኪዳን ሲሆን ከዚህ ቀጥሎ የምናነሳው ጾመ ነነዌና በመጀመሪያ ያየነው ማለትም ነገ ቅበላውን አድርገን ሐሙስ ኅዳር 15 ቀን ጀምረን ታሕሣስ 29 ቀን የምንፈታው ጾመ ነቢያት ነው።

ጾሙን ጾመሥርየት ጾመ ድኅነት ጾመ በረከት ያድርግልን።

ለብርሃነ ልደቱና ጥምቀቱ በሰላም ያድርሰን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።

 

የኔታ(ርእሰ ደብር ጥዕመ ልሳን፣

የስዊዘርላንድ ወረዳ ኃላፊ እና የጄኔቫ ደብረ መድኀኒት መድኃኔዓለም አስተዳዳሪ

ህዳር 12፣ 2015 (Nov 21, 2022)

የነብያት ጾም መግቢያ