Events Calendar

Sunday 04 December 2022
ቅዳሴ መርሐግብር
Sunday 04 December 2022, 07:00am
Hits : 49

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ። አሜን።

"ቅረቡ ኀቤሁ ወያብርህ ለክሙ፤ ወኢይትሐፈር ገጽክሙ።"

"ወደርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል። ፊታችሁም አይጨልምም"። መዝ ፴፫፥ ፭

የቅዳሴ ጥሪ

በክርስቶስ የተወደዳችሁና የተከበራችሁ በጄኔቫና አካባቢው የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የተዋህዶ ልጆች በሙሉ፥ በቅድሚያ እንኳን ሁላችንንም በቸርነቱ ጠብቆ ከዚህች ዕለትና ሰዓት በሰላም አደረሳችሁ። እሁድ ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ/ም (04/12/2022) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የጀ/አ/ሀ/ስ የጄኔቫ ደብረ መድኃኒት መድኃኔ ዓለም ቤ/ክርስቲያን ወርኀዊ መደበኛ የቅዳሴ መርሐ-ግብር ስላለ የበረከቱ ተሳታፊዎች እንድትሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተለመደ መንፈሳዊ ጥሪዋን ታቀርብላችዃለች። ከ05 am ሰዓት ጀምሮ የቤ/ክርስቲያኑ በር ክፍት ነው። የቅዳሴ መግቢያ ሰዓት 07am (ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ነው።)

የመድኃኔ ዓለም ቸርነት፤

የድንግል ማርያም አማላጅነት፤

የመስቀሉ በረከት በሁላችን ላይ ይደር።

አሜን።

 

ርእሰ ደብር ጥኡመ ልሳን የደብሩ አስተዳሪ

ቦታ፥
Charmilles Centre አካባቢ
Av d’Aire 3
1203 Genève

ቅዳሴ መርሐግብር