ስለ እኛ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ 

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 

 ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የጀርመንና አካባቢው ሊቀጳጳስ

ርእሰ ደብር ጥዑመ ልሳን ታከለ(የኔታ)

የስዊዘርላንድ ወረዳ ቤተ ክህነት ኃላፊና የጄኔቫ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ


 የጄኔቫ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም 

 

የደብረ መድሀኒት መድኃኔአለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በ2004 ዓ.ም በጥቂት ኢትዮጵያውያን ምእመናን ተመሰረተ፡፡

ብፁዕ አባታችን አቡነ ሕርያቆስ ታቦቱን ባርከው ደብሩን “የጄኔቫ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን” ብለው ሰይመውታል።  ቤተክርስቲያናችን ምንጊዜም ቢሆን የብጼዕነታችውን አባታዊ ውለታ አትዘነጋውም፤ በረከታቸው አይለየን እያለች ዘወትር በጸሎታቸን  ስናስባችው እንኖራለን። "እስመ ጸሎተ ጻድቅ ትክል ወታሠልጥ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ግዳጅ ትፈጽማለችና" ያዕ:5-16  እንዲል ሐዋርያው።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የዕምነቱ ተከታዮች በአቅራቢያ ያሉ ቤተክርስቲያናት እና አዳራሾችን በሰንበት ለጥቂት ሰዓታት በመከራየት የቅዳሴ ሥርዓትን እና የትምህርት አገልግሎትን በማካሔድ ላይ እንገኛለን፡፡

ቤተክርስቲያናችን በፍጥነት እያደገ ያለ ቤተክርስቲያን በመሆኑ ለምዕመኑ ለወጣቶች እና ለህጻናት ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለማዳረስና እንዲሁም ለሃገሩ አዲስ የሆኑ ወገኖቻችንን ለማለማመድ ጥረት እናደርጋለን።